የክህሎት ስልጠና እየተሰጠ ነው

ለሰው ሀብት አስተዳደር ሰራተኞች የክህሎት ስልጠና እየተሰጠ ነው::

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ልማት ም/ፕ/ጽ/ቤት በሁሉም ኮሌጆች ለሚገኙ የሰው ሀብት አስተዳደር ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች በዋናው ግቢ Cisco Lab ህንጻ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የእውቀትና የክህሎት ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት ተጀመረ።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአስ/ል/ም/ፕሬዚደንት ዶ/ር ሳሙኤል ጂሎ ስልጠናውን በተመለከተ ሲናገሩ የሰው ሀብት አስተዳደር መረጃዎችንና አሰራርን በኮምፒውተር የታገዘ በማድረግ ቀልጣፋ፣ ቀላል እና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት ከዩኒቨርሲቲው የአይ.ሲ.ቲ ባለሙያዎች ጋር በጋራ ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል። ይሄንን ዘመናዊ አሰራር ለመላመድና በቅልጥፍና ለመስራት የኮምፒውተር ፕሮግራሙን (ሶፍትዌሩን) ባበለጸጉ ባለሙያዎች ሀያ አምስት ለሚደርሱ ሰልጣኞች ስልጠናው መዘጋጀቱን ጠቁመው ሰልጣኞች ወደስራ ገበታቸው በሚመለሱበት ወቅት ስልጠናውን ላልወሰዱ ሰራተኞች እውቀታቸውን እንዲያጋሩ እንደሚደረግ ምክትል ፕሬዚደንቱ ተናግረዋል።

በዩኒቨርሲቲው የኮምፒዩተር ፕሮግራም አበልጻጊ (Software developer) የሆኑትና ስልጠናውን እየሰጡ ያሉት አቶ ደሣለኝ መንገሻ በበኩላቸው ቀደም ሲል የዩኒቨርሲቲውን የተማሪዎች መረጃ አያያዝ ስርዓት የዩኒቨርሲቲው የኮምፒውተር መተግበሪያ ማበልጸጊያ ቡድን (application development team) ማዘጋጀቱንና ውጤታማ ስራ መሰራቱን ገልጸው በአሁን ሰአት በዩኒቨርሲቲው ስር ያሉ ከአስር ሺህ በላይ የሚገመቱ ሰራተኞች መረጃ አዲስ ወደ በለጸገው የመረጃ ቋት እንዲገባ መደረጉን አብራርተዋል። የመረጃና አሰራር ስርዓትን ማዘመን የመረጃ ጥራትንና ደህንነትን ከማረጋገጡም ባሻገር የተቋሙን ቁመና የሚያሳድግ መሆኑን የገለጹት ባለሙያው ሰልጣኞች ተገቢውን ክህሎት እስኪጨብጡ ድረስ ስልጠናው በቀጣይ በስራ ቦታ ላይ በሚሰጥ ስልጠና (on Job training) ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et