ማስታወቂያ: የቅድመ ምረቃ መደበኛ እና የማታና እረፍት ቀናት መርሃግብር እጩ ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ

በኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠዉ የ2012 ዓ.ም የሁለተኛ ሴሚስተር ትምህርት ለማስጀመር የመልሶ ምዝገባ በበየነ መረብ ”Online” በሚከተለዉ መሠረት ይካሄዳል፡፡

  • የማታና የእረፍት ቀናት መርሃግብር ተመራቂ ተማሪዎች ምዝገባ ጥቅምት 19-24, 2013 . እንዲሁም የመደበኛ መርሃግብር ተመራቂ ተማሪዎችና የመደበኛ ፕሮግራም PGDT ሰልጣኞች ምዝገባ ጥቅምት 21-24 2013 . ይከናወናል።
  • ተመዝጋቢዎች በተማሪዎች መረጃ ቋት (SIS) ላይ በመግባት ለ2012 ዓ.ም ሁለተኛ ሴሚስተር ተመዝግባችሁ ለነበሩት ኮርሶች በድጋሜ ምዝገባ ማካሄድ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • የመደበኛ መርሀግብር ተመራቂ ተማሪዎች ጥቅምት 23-24 2013 ዓ.ም በየካንፓሶቻቸው መገኘት ይጠበቅባችሁዓል።
  • ለመደበኛ መርሀግብር ተመራቂ ተማሪዎች ትምህርት መልሶ መከፈትን በተመለከተ እና የCOVID -19 ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል ሊደረጉ ስለሚገቡ ጥንቃቄዎች ጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ገለፃ ይደረጋል፡፡ ዝርዝር መርሀግብሩ በየት/ቤቶችና በየትምህርት ክፍሎች ይገለፃል።
  • የመደበኛ መርሀግብር ተመራቂ ተማሪዎች የተመደባችሁበትን የዶርም ቁጥር ፣ የመመገቢያ አዳራሽና የተመደባችሁበትን ሴክሽን (Section) ከተማሪዎች የመረጃ ቋት (SIS) ላይ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
  • ትምህርት የሚጀመረው ለማታና የእረፍት ቀናት ተማሪዎች ጥቅምት 23 ቀን 2013 . ሲሆን ለመደበኛ መርሃግብር ተመራቂ ተማሪዎች ጥቅምት 26 2013 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

አጠቃቀሙን ለማግኘት ይህንን ይጫኑ

ማሳሰብያ፡-

  • የበየነ መረብ “Online” ምዝገባ ከላይ ከተጠቀሱት ቀናት ውጭ የማይሰራ መሆኑን እያሳወቅን የመደበኛ መርሃግብር ተመራቂ ተማሪዎች ከጥቅምት 23, 2013 ዓ.ም በፊት የሚመጡ ተማሪዎችን ዩኒቨርስቲዉ አያስተናግድም።
  • የበየነ መረብ “Online” እንዲመዘገቡ ከተፈቀደላቸው ተማሪዎች ውጭ ዩኒቨርስቲው የማይቀበል መሆኑን እናሳውቃለን። በምዝገባ ላይ ለሚያግጥሙ ችግሮች ሬጅስትራር ቢሮ ወይም የትምህርት ክፍላችሁን ሀላፊዎችን ከመምጣታችሁ በፊት በስልክ ወይም ባሉት የመገናኛ አማራጮች በመጠቀም ማሳወቅ ይጠበቅባችሁዓል።

   ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራርና አሉሚኒ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 887 1511 
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et