ማስታወቂያ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና አኪኮኖሚክስ ኮሌጅ አዋዳ ካምፓስ በ2013 ዓ/ም ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የትምህርት መስኮች በሁለተኛ ዲግሪ በእረፍት ቀን (Weekend) ተማሪዎች ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡

  1. MA in Community Development
  2. MA in Cooperative Development and Leadership
  3. MBA in Human Resource Management
  4. MBA in Marketing Management
  5. MSc in Economics (Tracks: Developmental Economics, Environmental Economics and Financial Economics)

 የማመልከቻ መስፈርቶች

  • ለሁለተኛ ዲግሪ አመልካቾች ከታወቀ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በተመሳሳይ ወይም በተዛማጅ የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ድግሪ ያለዉ/ያላት
  • አግባብነት ካላቸዉ ተቋማት 3 የድጋፍ ደብዳቤዎች ማቅረብ የሚችል/የምትችል
  • ዩኒቨርሲቲዉ የሚያወጣዉን የመግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችል/የምትችል
  • ቀደም ሲል ከተማሩበት የትምህርት ተቋም ኦፊሺያል ትራስክሪፕት ማስላክ የሚችል/የምትችል
  • አግባብነት ካላቸዉ ተቋማት የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችል/የምትችል

ማሳሰቢያ፡-

  • ምዝገባው የሚከናወነው በኦላይን ብቻ ሲሆን ምንም አይነት ማስረጃ በአካል ይዞ በመቅረብ ማስገባት አይቻልም፡፡
  • አመልካቾች ከጥቅምት 16-22 /2013 ዓ.ም የማመልከቻ ፎርሙን በዩኒቨርስቲው ድረገጽ (https://portal.hu.edu.et) አካውንት በመፍጠር አስፈላጊዎችን መረጃዎችን መሙላት ይጠበቅባቸዋል።
  • አመልካቾች የንግድ ባንክ ቁጥር 1000013481788 በመጠቀም የማመልከቻ ክፍያ 250 ብር  መክፈል ይጠበቅባቸል።
  • ክፍያዎትን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ማመልከቻ ፎርሙ በመመለስ ፒዲኤፍ (PDF) ፎርማት የተለወጠ የትምህርት ማስረጃዎትን፣ ባንክ የከፈሉበትን ደረሰኝ እና ሌሎች መረጃዎችን  በማማያዝ  ምዝገባዎትን ማጠናቀቅ ይኖርብዎታል፡፡
  • የመግቢያ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾ ከተማሩበት ተቋም ኦፊሺያል ትራስክሪፕታቸዉ ወደ ዩንቨርሲቲዉ ሬጅስትራርና አሉምናይ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ማስላክ የሚጠበቅባቸው ሲሆን በምዝገባ ወቅት ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ካልደረሰ መመዝገብ አይችሉም
  • የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ጥቅምት 27/ 2013 ዓ.ም በየኮሌጆቹ ይሆናል፡፡
  • የተማሪዎች ቁጥር ከመቀበል አቅም በታች (ዝቅተኛ) ከሆነ የትምህርት ፕሮግራሞች የማይከፈቱ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማስታወቂያዉን ለማዉረድ ይህንን ይጫኑ

ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራርና አሉሚኒ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et