የCOVID-19 (ኮሮና ቫይረስ) መስፋፋት አሳሳቢ መሆኑን በመገንዘብ ለሀዋሳ ዩኒቨሪሲቲ ማህበረሰብ የተላለፈ ጥብቅ መልዕክት!

የCOVID-19 (ኮሮና ቫይረስ) መስፋፋት አሳሳቢ መሆኑን በመገንዘብ ሀዋሳ ዩኒቨሪሲቲ 14/07/2012 በተደረገው የዓብይ ኮሚቴ ስብሰባ የሚከተሉትን ውሳኔዎች ለሁሉም ካምፓሶች አስተላልፏል፡፡

የተማሪዎች እንቅስቃሴን በተመለከተ

$11.  ተማሪዎች ስለCOVID19 ያላቸውን ግንዛቤ በተላያዩ መንገዶች በማሳደግ ከመንግስት እና ከጤና ባለሙያዎች የሚተላለፍላቸውን መመሪያዎች በጥብቅ ዲሲፕሊን መፈጸም አለባቸው፡፡

$12.  ተማሪዎች ከቀን 16/07/2012 ጀምሮ በምንም ዓይነት ምክንያት፤ ለምግብ፤ለሻይቡና እንዲሁም ወደ ቤተእምነቶች ለመሄድ ወይንም ለሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች ከጊቢ መውጣትም ሆነ፤ከውጭ ወደ ጊቢመግባት የማይችሉ መሆኑን ፡፡

$13.  በጊቢ ውስጥ ያሉ ፑል ቤቶች፡ ቲቪ መመልከቻ ክፍሎች፤የፖርት ማዘውተሪያዎች እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ተለይተው በልዩሁኔታ ፍቃድ ከሚሰጣቸው ላውንጆች እና ሻይ ቤቶች ውጪ፤ከቀን16/07/2012 ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የሚዘጉ መሆኑን፡፡

$14.  ሁሉም ተማሪዎች በተማሪዎች ካፍቴሪያ እንደየ ፍላጎታቸው ምግብ የሚመቻችላቸው ስለሆነ ምግብ ፍለጋ ወደ ውጪ መውጣት እንደማይፈቀድላቸው፡፡

$15.  ተማሪዎች በዶርም፤ በካፍቴሪያ፤እንዲሁም በቤተመፃሕፍቶች ማህበራዊ ርቀታቸውን በመጠበቅ የራሳቸውን እና የማኅረሰቡን ጤና መጠበቅ እንዳለባቸው፡፡

መምህራን እና የአስተዳደር ሠራተኞችን በተመለከተ

$11.  ከዚህ ቀደም ስለመማር ማስተማር የተላለፈው ውሳኔ እንዳለ ሆኖ፤ የአስተዳደራዊ ሥራ (Office holders)ከሚሠሩ academic staff ውጭ፤ ማንኛውም መምህር ከቀን 16/07/2012 ጀምሮ ወደ ጊቢ መግባት የተከለከለ መሆኑን እና መምህራን በያሉበት ሆነው በonline ተማሪዎቻቸውን ማገዝ እንዳለባቸው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የራሱን ዝርዝር መመሪያ የሚያወጣ ይሆናል፡፡

$12.  የአሰተዳደር ሰራቶኞችን በተመለከተ በቅርብ ቀን ግለፅ የሆነ መመሪያ የሚተላለፍ ሲሆን እስከዚያ ድረስ ግን ከመንግስት እና ከጤና ባለሙያዎች የሚተላለፍላቸውን መመሪያዎች በጥብቅ ዲሲፕሊን መፈጸም አለባቸው፡፡

በዩኒቨርሲቲ ካምፓሶች ቅጥር ጊቢ ውስጥ የሚኖረውን ማኅበረሰብ በተመለከተ

$11.  ጊቢ ውስጥ የሚኖረውን ማኅበረሰብ ቤተሰቡን በማስተማር እናበመምከርከ16/7/2012 ጀምሮ በራሱ መኖሪያ ቤት ውስጥ እንዲቆዩ ማድረግ አለበት፡፡ እንዲሁም ህጻናት ወደመጫወቻ ቦታዎች እና ስፖርት ሜዳዎች እንዳይሄዱ መከልከል አለበት፡፡

$12.  ከጊቢ መውጣትን በተመለከተ፤በጣም ላስፈላጊ እና መሰረታዊ የሆኑ የምግብ እናመድሐኒት ቁሳቁሶችን ለመግዛት ካልሆነ በቀር መውጣት የተከለከለ ይሆናል፡፡ ለጥየቃ የሚመጡ ቤተሰቦችን እና እንግዶችንም ማስገባት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲው የሚመጡ ባለጉዳዪች እና እንግዶችን በተመለከት

$11.  ከቀን 16/07/2012 ዓ.ምጀምሮማንኛውም እንግዳ (ባለጉዳይ)ወደዩኒቨሪሲቲጊቢየሚመጣ ከሆነ በልዩ ሁኔታ ከዩንቨሪሲቲ ከፍተኛ አመራር ፈቃድ ካላገኘ ወደ ጊቢ መግባትአይችልም፡፡

በመጨረሻም፤ትኩሳት፤ለመተንፈስ መቸገር፤የትንፋሽ መቆራረጥ እና ሳልካገጠመ ወይንም ይህንን ምልክት የሚያሳይ ተማሪ ካለ በነፃ ስልክ መሥመር 6929 ለደ/ብ/ብ/ሕ/ክ ጤና ቢሮ ጥቆማ መስጠት ይቻላል ይህ ካልሆነ ለተማሪዎች ክልኒክ ማሳዎቅ አለበት፡፡

$1v  መዘናጋት ዋጋ ያስከፍላል! በመተባበር፤በመደማመጥ እና የሚሰጡ መመሪያዎችን በስነምግባር በመፈፀም ይህንን ወቅት ማለፍ እንችላለን!!!

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ

Newsletter

Make sure you dont miss interesting happenings by joining our newsletter program.

Contact us

Armaye Assefa
Director, Corporate Communication & Marketing Directorate

  • Phone: +251462200341/+251462209331/+251462212720

Connect with us

We're on Social Networks.
Follow us & get in touch.