የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ካስኬፕ ፕሮጀክት በሲዳማ ዞን የአርሶ አደሮች የመስክ በዓል አከበረ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ካስኬፕ ፕሮጀክት በሲዳማ ዞን ጎርቼ ወረዳ አርቤ ሁልበቶ ቀበሌ የአርሶ አደሮች የመስክ በዓል ከአጋር አካላት ጋር በመተባብር በህዳር 15/2011ዓ.ም በማዘጋጀት የመስክ ምልከታ አካሄደ፡፡

ዶ/ር በየነ ተክሉ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ካስኬፕ ፕሮጀክት ማናጀር በበዓሉ መክፈቻ ላይ ዩኒቨርሲቲው ባለፉት ስምንት አመታት በክልሉ 13 ወረዳዎች ላይ በርካታ የምርምርና ቴክኖሎጂን የማስተሳሰር ፣የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ፣ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እና ተስማሚ ቴክኖሎጂዎችን የማቅረብ ስራዎችን በስንዴ፣በበቆሎ ፣በቢራ ገብስ፣በገብስ፣በእንስሳት ሃብት ፣በተፈጥሮ ሃብት እና በመሳሰሉት ላይ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

ዶ/ር በየነ ቀጥለውም የዛሬውም በዓል ለዚህ ወረዳ አዲስ ቢሆንም በሌሎች ወረዳዎች ተሞክሮ ውጤታማ የሆነውን የብቅል ገብስ ላይ በመመራመርና ውጤቱንም ለአርሶ አደሮቹ የማስተዋወቅና የተገኙትንም ተሞክሮዎች በቅድመ ማስፋትና በማስፋት በዚሁ ወረዳ በአርሶ አደሮቹ በኩል የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፣ አርሶ አደሩ ለኢንዱስትሪው ጥሬ ዕቃ አቅራቢ እንዲሆን ማስቻል እና የአርሶ አደሩን የኑሮ ሁኔታ በሂደት ለመቀየር የሚያስችል የምርምር ውጤቶችን ማሳያ ሲሆን አርሶ አደሮቹም ቴክኖሎጂዎችን በማስቀጠሉ ድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

ዶ/ር በየነ አክለውም አርሶ አደሮቹ ይሄንን የምርምር ውጤት ተሞክሮ በማየት አንዱ ከአንዱ ልምዱን እና ክህሎቱን በመቅሰም ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ ፕሮጀክቱንና ባለድርሻ አካላትን መደገፍ እንዳለባቸው ያሳሰቡ ሲሆን ከዚሁ ጎን ለጎንም ከሴት አርሶ አደሮች ጋር በጋሮ አትክልት ዙሪያ አብረን እንሰራለን ብለዋል፡፡

አቶ አበራ መኮንን በኦሮሚያ ክልል ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌደሬሽን የአሰላ ብቅል ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ እንደገለጹት ፋብሪካው ብቅል ከፈረንሳይ እና ቤልጀም በርካታ የውጭ ምንዛሪ በማውጣት የሚያስመጣ ሲሆን በሀገር ውስጥ መመረት መጀመሩ እንደ ሃገርም የውጭ ምንዛሪን ያስቀርልናልና በቀጣይም ተጠናክሮ መሰራት አለበት ብለዋል፡፡

በዕለቱም የፕሮጀክቱ ተመራማሪዎች ለአርሶ አደሮቹ እና ለተጋባዥ እንግዶች በአርሶ አደሮቹ ማሳ ላይ በምርምር ውጤቶቹ ዙሪያ ገለጻ በማድረግ የጉብኝቱ ፕሮግራሙ የተካሄደ ሲሆን አርሶ አደሮቹም ባዩት ነገር ደስተኛ እንደሁኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Newsletter

Make sure you dont miss interesting happenings by joining our newsletter program.

Contact us

Armaye Assefa
Director, Corporate Communication & Marketing Directorate

  • Phone: +251462200341/+251462209331/+251462212720

Connect with us

We're on Social Networks.
Follow us & get in touch.