በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የበንሳ ዳዬ ካምፓስ ተማሪዎችን በመቀበል በይፋ ሥራ ጀመረ

አዲስ የተከፍተውና ላለፉት 4 ዓመታት በግንባታ ሂዳት ላይ የነበረው የበንሳ ዳዬ ካምፓስ ጥቅምት 30/2011ዓም ወደ ካምፓሱ ለተመደቡ 340 አዲስ ገቢ ተማሪዎች በአከባቢው ማኀበረሰብ ደማቅ አቀባበል የተደረገ ሲሆን የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አቶ አያኖ በራሶ በቦታው በመገኘት በስተላለፉት መልዕክት መንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በያዘው የትኩረት አቅጣጫ ካምፓሱ የተገነባ ሲሆን ሙሉ በሙሉ ባይጠናቀቅም የሰው ሃይልና አስፈላጊ ቁሳቁሶች በመሟላታቸው ወደ ስራ መገባቱን አስረድተዋል፡፡

የበንሳ ዳዬ ካምፓስ ካለው ርቀትና የመሬት አቀማማጥ አኳያ ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ራሱን ወደቻለ ዩኒቨርሲቲ ልያድግ የሚችል በመሆኑ ግንባታዎቹ ይህንኑን ታሳቢ አድርጎ የተካሄዱ እንደሆነ ያስታወቁት ፕሬዝዳንቱ ተማሪዎችም ፤ ሰራተኞችና የአከባቢው ማኀበረሰብ እንደግል ንብረታቸው መንከባከብና ለመጭው ትውልድ የማስተላፍ ግዴታ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

አዲስ የተመደቡ ተማሪዎችም ከቤተሰብ ተለይተው የመጡበትን ዓላማ በማንገብ ጊዜያዊ ተግዳሮቶችን በመቋቋም፤ ከአልባሌ ሱሶች በመራቅና በርትቶ በማጥናት ከቤተሰብና ሀገር የተጣለባቸውን አደራ ለመወጣት ራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡

የካምፓሱ ማኔጅንግ ዳይሬክቴር አቶ ገነነ ካቢሶ በበኩላቸው ካምፓሱ በእርሻ ሜካናይዜሼንና በመምህራን ስልጠና የትምህርት መስኮች ተማሪዎችን ተቀብሎ የሚያሰለጥን ሲሆን በተማሪዎቹ በሚካሄዱ አሳታፊና ችግር ፌች ምርምሮች የአከባቢውን ማሀበረሰብ ያሳተፈ እንዲሆን ህብረተሰቡ እንዲተባበር ተከታታይ ስልጠናዎች የሚሰጡ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

በስነ ስርዓቱ ላይ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንቶች የበንሳ ዳዬ ከተማ ፤ የአከባቢው ቀበሌ ገበሬ ማኀበራት አመራሮች፤ የሀገር ሽማግሌዎች፤ የሃይማኖት አባቶችና ከአከባቢው ማኀበረሰብ የወጣቶችና ሴቶች ተወካዮች መገኘታቸው ታውቋል፡፡

Newsletter

Make sure you dont miss interesting happenings by joining our newsletter program.

Contact us

Armaye Assefa
Director, Corporate Communication & Marketing Directorate

  • Phone: +251462200341/+251462209331/+251462212720

Connect with us

We're on Social Networks.
Follow us & get in touch.