የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ካስኬፕ ፕሮጀክት በጉራጌ ዞን የአርሶ አደሮች የመስክ በዓል አከበረ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ካስኬፕ ፕሮጀክት የአርሶ አደሮች የመስክ በዓል በጉራጌ ዞን በቸሃና ጉመር ወረዳዎች ከአጋር አካላት ጋር በመተባብር በህዳር 1/2011 ዓ.ም አከበረ፡፡

ዶ/ር ተስፋዬ አበበ  የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ  ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ጽ/ቤት ፕሬዚዳንት በበዓሉ መክፈቻ ላይ ዩኒቨርሲቲው ባለፉት ስምንት አመታት በዚሁ ወረዳ በርካታ የምርምርና ቴክኖሎጂን የማስተሳሰር ፣የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ፣ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እና ተስማሚ ቴክኖሎጂዎችን የማቅረብ ስራዎችን በስንዴ፣በበቆሎ ፣በቢራ ገብስ፣በገብስ፣በእንስሳት ሃብት ፣በተፈጥሮ ሃብት እና በመሳሰሉት ላይ እየሰራ ሲሆን የዛሬውም በዓል የበቆሎና የቢራ ገብስ ላይ በመመራመርና ውጤቱንም ለአርሶ አደሮቹ የማስተዋወቅና የተገኙትንም ተሞክሮዎች በቅድመ ማስፋትና በማስፋት በዚሁ ወረዳ በአርሶ አደሮቹ በኩል የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፣ አርሶ አደሩ ለኢንዱስትሪው ጥሬ ዕቃ አቅራቢ እንዲሆን ማስቻል እና የአርሶ አደሩን የኑሮ ሁኔታ በሂደት ለመቀየር የሚያስችል የምርምር ውጤቶችን ማሳያ ሲሆን አርሶ አደሮቹም ቴክኖሎጂዎችን በማስቀጠሉ ድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

View the embedded image gallery online at:
http://hu.edu.et/hu/index.php/news/610-%E1%8B%A8%E1%88%80%E1%8B%8B%E1%88%B3-%E1%8B%A9%E1%8A%92%E1%89%A8%E1%88%AD%E1%88%B2%E1%89%B2-%E1%8A%AB%E1%88%B5%E1%8A%AC%E1%8D%95-%E1%8D%95%E1%88%AE%E1%8C%80%E1%8A%AD%E1%89%B5-%E1%89%A0%E1%8C%89%E1%88%AB%E1%8C%8C-%E1%8B%9E%E1%8A%95-%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%88%AD%E1%88%B6-%E1%8A%A0%E1%8B%B0%E1%88%AE%E1%89%BD-%E1%8B%A8%E1%88%98%E1%88%B5%E1%8A%AD-%E1%89%A0%E1%8B%93%E1%88%8D-%E1%8A%A0%E1%8A%A8%E1%89%A0%E1%88%A8.html?tmpl=component&print=1&layout=default&page=#sigFreeId20bb48b95c

ዶ/ር በየነ ተክሉ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ካስኬፕ ፕሮጀክት ማናጀር ፕሮጀክቱ ባለፉት ዓመታት በ13 ወረዳዎች ላይ የግብርናውን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በርካታ የምርምር ስራዎችን በክልሉ እየሰራ መሆኑን የገለጹ ሲሆን የዛሬውም ጉብኝት ፕሮጀክቱ በቅድመ ማስፋት ስራዎች በጉመርና ቸሃ ወረዳዎች በበቆሎና የቢራ ገብስ ላይ የሰራቸውን ምርምሮች ለአርሶ አደሮቹ የማስተዋወቅ ፕሮግራም ነው ብለዋል ፡፡

የመስክ ጉብኝቱን ሙሉ ቪዲዮ ከስር ይመልከቱ።

ዶ/ር በየነ አክለውም አርሶ አደሮቹ ይሄንን የምርምር ውጤት ተሞክሮ በማየት አንዱ ከአንዱ ልምዱን እና ክህሎቱን በመቅሰም ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ ፕሮጀክቱንና ባለድርሻ አካላትን መደገፍ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

በዕለቱም የፕሮጀክቱ ተመራማሪዎች ለአርሶ አደሮቹ እና ለተጋባዥ እንግዶች በአርሶ አደሮቹ ማሳ ላይ በምርምር ውጤቶቹ ዙሪያ ገለጻ በማድረግ የጉብኝቱ ፕሮግራሙ የተካሄደ ሲሆን አርሶ አደሮቹም ባዩት ነገር ደስተኛ እንደሁኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

በስለሺ ነጋሽ