በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ከ400ሺ በላይ ሀገር በቀል የዛፍ ችግኞችን ለህብረተሰቡ ማከፋፈሉን አስታወቀ፡፡
- Details
- Category: News
- Published on 12 October 2018
- Hits: 1326
የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ግርማ አማንቴ እንዳስታወቁት የችግኞቹ መሰራጨት በአሁኑ ወቅት በሀገር አቀፍ ደረጃ ጎልቶ የምታየውን የአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያያዥ የሆኑ ችግሮችን ከማቃለል በተጨማሪ ሀገር በቀል የዛፍ ዝሪያዎችን ጠብቆ ለማቆየት ከፍተዋኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡
በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን እና በአጎራባች ኦሮሚያ ወረዳዎች በተለይም በስራሮ፤አጄና አርስነገሌ ወረዳዎች በግል አርሶአደሮች፤ መንግስታዊና መንግሰታዊ ባልሆኑ ተቋማት አማካይነት ተከላው መከናወኑን ከገለፃው ለመረዳት ተችሏል፡፡
በኮሌጁ የአካደሚክ ጉዳዮች ተባባሪ ዲን አቶ ግርማ መኩሪያ በበኩላቸው ኮሌጁ በተያዘው 2011 የትምህርት ዘመን ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ 3ኛዲግሪ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅት ማጠናቀቁን ጠቁመው በተለይም በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያ የሆነውን የትምህር ፐሮግራም በአየር ንብረት ለውጥ ለይ በዶክትሬት ዲግሪ ተጨማሪ ተማሪዎችን ለመቀበል መዘጋጀቱን አስረድተዋል፡፡
ለተማሪዎች በተግባር የተደገፈ ትምህርት የሚሰጥበትን አሰራር ለማጠናከር አዳዲስ የቤተ ሙከራ፤የመማሪያ ክፍል ግንባታዎች መጠናቀቃቸውን ገልፀው በየትምህርት ክፍሎች በሚደገፉ የሙከራ ስራዎች የአከባቢው አርሶ አደሮች ከምግብ ሰብል በተጨማሪ የዓሣ ጫጩቶችን ተቀብለው በሰው ሰራሽ ኩሬዎች በማርባት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተደረገ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡