የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ምርመራና የግንዛቤማስጨበጫ ስልጠና ሠጠ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና ና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የምርምርና ማህበረሰብ ጽ/ቤት የማህበረሰብ ቀንን አስመልክቶ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ማለትም የደምግፊት፣የስኳር ናከመጠንያለፈ ውፍረት ላይ ምርመራና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በሀዌላ ቱላ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለአካባቢው ማህበረሰብ በ13/9/10ዓ.ም ሰጠ፡፡

127A7543

አቶ አለሙ ጣሚሶ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ምንም እንኳን አስከፊ ቢሆኑም መከላከልና መታከም የሚቻል መሆኑን ማህበረሰቡ ባለማወቁ በበሽታዎቹ እየተጠቃ ስለሆነ በዚህ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለህብረተሰቡ መስጠት አስፈላጊ በመሆኑ ፕሮግራሙ መዘጋጀቱን ገልጸው በቀጣይም ከህብረተሰቡ ጋርበቅርበት እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡

አቶ አየለ አደቶ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ በዕለቱ ተገኝተው ዩኒቨርሲቲው ከሚሰራቸው ስራዎች አንዱ የተለያዩ ምርምሮች በማድረግ በህክምናው ዘርፍም ማህበረሰቡን ማገልገል ሲሆን የዛሬው ምፕሮግራም ጤናማ ህብረተሰብን ለመፍጠር ቅድመ ግንዛቤ በማስጨበጥ እራሱን ከበሽታ እንዲከላከል የሚረዳና ማህበረሰቡ ለአካባቢው ልማትና ብልጽግና መሰረት እንዲሆን የሚያስችል ስልጠና ነው ብለዋል፡፡

በዕለቱ ስለበሽታዎቹ በህክምና ባለሙያዎች ስልጠና ከተሰ ጠ በኃላ የደምግፊት፣ ስኳርና በውፍረትና ቁመት ልኬት መመጣጠን ላይ ለተሳታፊዎች ምርመራ ተደርጎ የማማከር አገልግሎት ተከናውኗል፡፡

 

 በስለሺ ነጋሽ

 

Newsletter

Make sure you dont miss interesting happenings by joining our newsletter program.

Contact us

Armaye Assefa
Director, Corporate Communication & Marketing Directorate

  • Phone: +251462200341/+251462209331/+251462212720

Connect with us

We're on Social Networks.
Follow us & get in touch.