የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ ማሰባሰቢያና ማስወገጃ መሳሪያዎች አስረከበ

HU013166

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምርምርናቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕ/ጽ/ቤት የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከዶንኪ ሳንክችዋሪ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በሀዋሳ ከተማ በደረቅ ቆሻሻ ማሰባሰቢያና ማስወገጃ የአህያ ጋሪ ላይ የሚሰሩ ሰራተኞችንና የአህዮችን ደህንነት ማሻሻል በሚል የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክት ተግባራዊ በማድረግ እስካሁን የተሰሩ ስራዎችን ማለትም ዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ ማሰባሰቢያና ማስወገጃ የአህያ ጋሪዎች እና ሌሎች ተያያዥ መሳሪያዎችን ለሀዋሳ ከተማ ማዘጋጃ ቤትና በፕሮጀክቱ ታቅፎ ሲሰራ ለቆየው የሀዋሳ ውበት የደረቅ ቆሻሻ አስወጋጅ ማህበር የርክክብ ስነ-ስርዓት አርብ ነሐሴ 11/2010 ዓ.ም አካሄደ፡፡

 

አቶ አያኖ በራሶ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በመክፈቻ ንግግራቸው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማሩ በተጨማሪ የአካባቢ ማህበረሰብን ሊያገለግሉ የሚችሉ ምርምሮችን በማካሄድ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ ሲሆን የዛሬውም የምርምርና የቴክኖሎጂ ውጤት ውቢቷን ሀዋሳ የበለጠ ውብ እንድትሆን የሚረዳ፣የንጽህና ስራ ለሚሰሩትም የስራ እድል ከመፍጠሩም በተጨማሪ ጤንነታቸው እንዲጠበቅ የሚረዳ እና የእንሰሶቹንም ጤንነት የሚጠብቅ በመሆኑ ረዥም ጊዜ ልንገለገልባቸው ይረዳናል ብለዋል፡፡

በዕለቱም ተመራማሪዎች የተለያዩ ጥናቶችን ያቀረቡ ሲሆን ተሳታፊዎችም የተውጤቶችና መሳሪያዎች ለከተማው ጽዳት በተለይ ደግሞ የአጽጅዎችን እና የእንሰሳዎቹን ጤንነት የሚጠብቅ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲ እና ባለድርሻ አካላትን ላደረጉት ትብብር አመስግነዋል፡፡

(በስለሺ ነጋሽ)

Hawassa University is undergoing a Councel Meeting.

Hawassa University is undergoing a Councel Meeting. 

The following pictures show the meetings.


 

Newsletter

Make sure you dont miss interesting happenings by joining our newsletter program.

Contact us

Armaye Assefa
Director, Corporate Communication & Marketing Directorate

  • Phone: +251462200341/+251462209331/+251462212720

Connect with us

We're on Social Networks.
Follow us & get in touch.