የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ ኢ.ፍ.ድ.ሪ የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ-ካርታ ዙሪያ ውይይት አካሄደ

moe2011 1

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከመስከረም 09/2011. ጀምሮ ለሶስት ቀናት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናዉ ግቢና በየኮሌጆቹ ለመምህራንና አስተዳደር ሠራተኞች ... የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ-ካርታ ዝግጅትና የሪፎርም ሀሳቦች ላይ የውይይት መድረክ አደረገ፡፡

moe2011 2

የተዘጋጀውን ጥናት የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፤ በጥናቱ የተሳተፉ ምሁራን እነዲሁም ስልጠና በወሰዱ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች ከቀረበ በኃላ ከተሳታፊዎች ጋርም የነቃ ተሳትፎና ውይይት የተደረገ ሲሆን የኢ... ትምህርትና ስልጠና ፍኖተ-ካርታ ለዘላቂልማት ግቦች መሳካት ስለሚኖረው ሚናም ጥልቅ የሆነ ውይይት ተደርጓል፡፡

ተሳታፊዎችም በአፈፃፀሙ ላይና አንዳንድ ግልጽ ባልሆኑ ነጥቦች ላይ ጥያቄዎችን በማንሳት እና ጠቃሚ የሆኑ ሀሳቦችን በመስጠት የተሳካ ውይይትአካሂደዋል፡፡

የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ አበረከተ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በጨፌ ኮቲጀቤሳ ለሚገኙ 507 ተማሪዎች ለ2011 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለተማሪዎቹ የመማሪያ እና መገልገያ የሚሆኑ የመማሪያ ቁስቁሶች በጨፌ ኮቲጀቤሳ 1ኛ እና መለስተኛ ትምህርት ቤት አበረከተ፡፡

አቶ ዮሃንስ ዮና የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በወቅቱ እንደተናገሩት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በርካታ ስራዎችን እየሰራ ያለ ሲሆን የዛሬውም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ከኤስ.ኦ.ኤስ የህፃናት መንደር ሀዋሳ ፕሮግራም ጋር በመተባበር በተለያዩ ምክንያቶች ትምህርታቸውን መከታተል ያልቻሉና ያቋረጡ ተማሪዎችን በጥናት ለመለየት በመቻሉ በቱላ ክ/ከ ጨፌ ኮቲጀቤሳ ቀበሌ ውስጥ ለሚገኙ ለችግር የተጋለጡ ህፃናትንና ቤተሰብን በትምህርትና አቅም ለማጎልበት ለ3ኛ ጊዜ የተበረከተ የመማሪያ ቁስቁሶች ናቸው ብለዋል፡፡

አቶ ዮሃንስ አክለውም ይህ ፕሮግራም ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ለ5ዐ7 ተማሪዎች ሁለት ጊዜ ድጋፍ በማድረግ ትምህርታቸውን እንዲማሩ ያስቻለ ሲሆን ልጆቹ በአግባቡ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ በመነሻ ጥናትና የቤተሰቡ የዕድገት ዕቅድ ጥናት ታይቶ ወላጆቻቸውን መደገፍ አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት የተለያዩ ድጋፎችና ለሃያ አምስት እማወራዎች ለእያንዳዳቸው አስር ምርጥ የዶሮ ዝርያዎችን ከሃምሳ ኪሎ ግራም መኖ ጋር በከዚህ በፊት ማከፋፈላቸውን ገልፀዋል፡፡

(በስለሺ ነጋሽ) 

Newsletter

Make sure you dont miss interesting happenings by joining our newsletter program.

Contact us

Armaye Assefa
Director, Corporate Communication & Marketing Directorate

  • Phone: +251462200341/+251462209331/+251462212720

Connect with us

We're on Social Networks.
Follow us & get in touch.