በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ድጋፍ የተቋቋሙት የዶሮ እርባታ ማዕከላት ተመረቁ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕ ጽ/ቤት ባስሩ በሚገኘው የማህበረሰብ አገልግሎት ጽ/ቤት በሀዋሳ ከተማ፣ በሀዋሳ ዙሪያና በሲዳማ ዞኖች ለሚገኙ ስራ አጥ ወጣቶች የዘመናዊ የዶሮ እርባታ ማዕከላትን አቋቁሞ ከሚያዝያ 3-4/2006 ዓ.ም አስመረቀ፡፡

DSC 0370ሚያዝያ 3/2006 ዓ/ም በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በታቦር ክፍለ ከተማ እና በቱላ ክፍለ ከተማዎች የተቋቋሙትን የዶሮ እርባታ ማዕከላት ለማስመረቅ የደብብ/ብ/ብ/ህ/መ ግብርና ቢሮ ኃላፊና የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ተወካይ አቶ አስፋው ጎኔሶ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡ እሳቸው እንደተናገሩት የአምስት ዓመቱን የእድገትና ትራስፎርሜሽን እቅድ ለማሳካት የግብርና ኢኮኖሚው ዘርፍ ወሳኝ ነው፡፡ ይህንንም ለማሳካት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የጎላ ሚና አላቸው ብለዋል፡፡ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ወጣቶችን በተለያዩ የስራ ዘርፎች አስልጥኖ በክህሎት የበቁ ለማድረግና ወደ ስራ እንዲገቡ እያደረገ ያለው ጥረት የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ድጋፍና ክትትሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕ የሆኑት አቶ አያኖ በራሶ በምረቃው በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር ዩኒቨርሲቲው የተማረ የሰው ሀይልን ከማፍራት ጎንለጎን የመንግስትን ስትራቴጂ ለማሳካት ዘርፈ ብዙ የማህበረሰብ አግልግሎት ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ በተለይም ስራ አጥነትን ከመቅረፍና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ከማስተዋወቅ አንፃር አመርቂ ስራዎችን እየስራ ይገኛል ብለዋል፡፡ አቶ አያኖ አክለውም ዩኒቨርሲቲው በስሩ የተቋቋሙትን የቴክሎጂ መንደሮች በገንዘብም ይሁን በተለያዩ የአቅም ማጎልበት ስልጠናዎች የማብቃት ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው በቀጣይም ብዙ ሊሰራባቸው የሚገባ ዘርፎችን በመለየት ከወትሮው በተለየ እንደሚሰራ አብራርተዋል፡፡

ዶ/ር ተስፋዬ አበበ የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕ ጽ/ቤት እያከናወናቸው ያለውን ስራዎች ባብራሩበት ወቅት እንዳሉት፤ በተለያዩ ዘርፎች፤ ለአብነት በእንጉዳይ አመራረት፣ በንብ ማነብ፣ በሽፈራው (ሞሪንጋ) ተክል አበቃቀልና አጠቃቀም፣ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰሩ ያሉትን ስራዎችም አመርቂ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል፡፡

ዶ/ር ተስፋዬ አከለው እንዳብራረቱት በሁለቱም ቀናት የተመረቁት የዶሮ እርባታ ማዕከላት እያንዳዳቸው የክህሎት ስልጠናን፣ የቤት መስሪያን፣ የጫጩት መግዥያና የሶስት ወር መኖን ጨምሮ ለእያንዳንዳቸው አራት መቶ ሺህ ብር በአጠቃላይ ለአምስቱም የዶሮ እርባታ ማዕከላት ሁለት ሚሊዮን ብር ያህል ዩኒቨርሲቲው ድጋፋ ማድረጉንም አክለው ገልጸዋል፡፡

በሀዋሳ ከተማ ያሉት የዶሮ እርባታ ማህበራት በከተማው ያለው የእንቁላል ፍላጎት ከፍተኛ በመሆኑ ዶሮዎችን ተንከባክበው በማሳደግ ለገበያ እንቁላል እንደሚያቀርቡና በሀዋሳ ዙሪያ ዶሬባፋና በቦርቻ ወረዳ ይርባ ከተማ እንዲሁም ዳሌ ወረዳ ይርጋለም አካባቢ ያሉት ማህበራት የሶስት ወር ጫጩቶችን ለአርሶ አደሩ በመሸጥ እንደገና ከደብረዘይት የግብርና ምርምር ተቋም የአንድ ቀን ጫጩቶችን አምጥተው በማሳደግና ለመሸጥ ማሰባቸውን ገልጸዋል፡፡

DSC 0421ወጣት ነጻነት ብርሃኑ በሃዋሳ ከተማ ከተቋቋሙት የዶሮ እርባታ ማዕከላት አንዱ በሆነው የአኩኩሉ ዶሮ እርባታ ማህበር ሊቀመንበር እንደገለፀው፣ ዩኒቨርሲቲው እያደረገው ያለው ድጋፍ የሚደነቅ መሆኑን ገልጾአል፡፡ ወጣቱ አከሎም የእንድ ቀን ጫጩት አሳድገው የሶስት ወር ቄብዶሮዎች እንዲሆኑ ለማድረግ ሁሉም የማህበሩ አባላት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ የቆዩ መሆኑንና በሁሉም ወጣቶ በኩል ከፍተኛ መነሳሳትና የስራ ባህላቸውም ጭምር እየተለወጠ እንዳለ ገልፆአል፡፡ ዩኒቨርሲቲው የሰጣቸው መኖ ሊያልቅ መቃረቡ፣ የመብራትና ውሃ ችግር ፈታኝ ተግዳሮቶች እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ የሚመለከተው አካል በተለይም የከተማው ግበርና ጽ/ቤት ድጋፍና ክትትል እንዲያደርጉላቸውም አሳስቧል፡፡

ከሀዋሳ ከተማ የጀመረው የዘመናዊ የዶሮ እርባታ ማዕከላት የምረቃ በዓል በሀዋሳ ዙሪያ ዶሬባፋና የሚገኘውን አጁጃ የዶሮ እርባታ ማህበር፣ በቦርቻ ወረዳ የሚገኘው በሱስም የዶሮ እርባታ ማህበርና በዳሌ ወረዳ በይርጋለም ከተማ የተቋቋመውን ኤልቶ የዶሮ እርባታ ማህበራት ተመርቀው ለሚመለከታቸው አካልና ለግህበራቱ ተላልፈው ተስጥተዋል፡፡

በሀዋሳ ከተማ፣ በሀዋሳ ዙሪያ፣ በቦርቻና ዳሌ ወረዳዎች በተካደው የምረቃ በዓል ላይ የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ አክሊሉ አዶላ፣ የሲዳማ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ የሆኑት አቶ መምሩ ሞኬ፣ የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊና የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ተወካይ አቶ አስፋው ቦነሳ፣ የወረዳና የክፍለ ከተማ አስተዳዳሪዎች፣ የዩኒቨርሲቲው የበላይ አመራር አካላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

 

 

በወንድማገኝ ተስፋዬ

አርታኢ፡ መልሰው ደጀኔ

Hawassa University (HwU) hosts the 9th TB Research Conference (9th TRAC)

tb day banner2Hawassa University hosted the 9th TB research Annual conference (TRAC) and world TB day in collaboration with TRAC Secretariat, Federal Ministry of Health and SNNPR Health Bureau March 21-24, 2014 with a theme ‘Let the community move: Use diverse community experience to curb TB epidemic’ in the presence of His Excellency Dr. Kebede Worku State Minister FMoH, Dr. Yosef Mamo, President of HwU,  H.E. Mr. Kifle Head, SNNPR Health Bureau and Vice President of the Regional State, Mr. Denis Weller, USAID Mission Director in Ethiopia, Mr. Tewodros Gebiba, Deputy Mayor of Hawassa City, representatives from WHO, USAID, CDC, AHRI, TB CARE, GOS and NGOs. 

During the opening session Welcome Notes were made by Dr. Yosef Mamo, H.E. Mr. Kifle and Mr. Tewodros Gebiba; Mr. Denis Weller, WHO and CDC representatives made Key Note addresses.  H.E. Dr. Kebede Worku made an opening speech.  

DSC 1174In his address during the conference held at HwU’s Training Center, where about 550 participants were on attendance, Dr. Yosef Mamo said the conference creates a wonderful opportunity for sharing and disseminating locally proven experiences and research outputs of currency for Tuberculosis (TB) prevention and control activities in Ethiopia. He added, this conference deepens our understanding of TB, improve our ability to fight and control the transmission of Tuberculosis. Moreover , president Mamo highlighted, we should play a significant role in curbing the epidemic by actively involving the community in every endeavor as conveyed by the theme of this year’s annual conference - ’Let the community move: use diverse community experience to curb TB epidemic’.   

In addition, President Mamo stressed, the conference was a good platform to make useful contacts for future cooperation and networking so as to share experiences and develop collaborations at personal and institutional level. Moreover, improved cooperation, information transfer, technology development and research are important tools that we need to make use of to find solutions to our common welfare and development challenges like TB.

DSC 1218In this special event where policy makers, academia and researchers convened, His Excellency, Dr. Kebede Worku (State Minister of Health)made an opening speech. According to him, the Federal Democratic Republic of Ethiopia Ministry of Health has been working to prevent and eradicate TB and TB related diseases through different strategies and high community mobilization. Ministry of Health, H.E. added, is eager to provide quality health services and qualified health professionals. He also indicated that, Ethiopia is one of the 22 high TB burden countries.  According to him, more than 3338 governmental and 249 private health sectors are operational at national level. He also noted that, now a day, the prevalence rate of TB is declining thanks to government commitment and the efforts by Health Extension workers.

His Excellency appreciated Hawassa University and Southern Nations Regional Health Bureau and governmental and non-governmental organizations who contributed for the success of this historic conference. He underlined the importance of boosting our endeavors and strengthening our commitment   to curb the epidemic.

In his Welcome Note, H.E. Mr. Kifle in his part addressed the TB community who participated in the 9th TRAC and underlined the need to strengthen networking among researchers and policy makers in awaking the community. He highlighted the importance of community awareness and education in the fight against MDR TB.

tb conDuring this special event more than 85 research and poster presentations were made documenting research findings on TB and MDR TB by junior and senior researchers. International experiences were also presented from Tanzania and Zimbabwe.

Two best abstract and one best poster awardees received special award from H.E. Dr. Kebede Worku. Hawassa University was also awarded a trophy for organizing such a colorful conference.

Question and Answer competitions among Hawassa University students and faculty organized by Tamesol communication in collaboration with ETV was also part of the TB Day event. The event was concluded with a public walk event in Hawassa City adorned by the Region’s police March band. 

 

 

 By Wondimagegn Tesfaye

Newsletter

Make sure you dont miss interesting happenings by joining our newsletter program.

Contact us

Armaye Assefa
Director, Corporate Communication & Marketing Directorate

  • Phone: +251462200341/+251462209331/+251462212720

Connect with us

We're on Social Networks.
Follow us & get in touch.