ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ የቅድመ ዝግጀት እና መከላከል ሥራዎችን በመሥራት ላይ ይገኛል

Rate this item
(0 votes)

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ የቅድመ ዝግጀት እና መከላከል ሥራዎችን በመሥራት ላይ ይገኛል

ይንንም ተግባር ከሳይንስ እና ከፍተኛ ት/ት ሚኒስተር አቅጣጫ ከተሠጠበት ዕለት ጀምሮ በዩኒቨርሰቲው ፕሬዝዳንት የሚመራ እና የዩኒቨርሰቲውን ምክትል ፕሬዝዳንቶች እና ሌሎች አመራሮችን የያዘ ዓብይ ኮሚቴ በማዋቀር ሥራ ጀምሯል፡፡

ዓብይ ኮሚቴው ሁለት ንዑሳን ኮሚቴዎችን ያዋቀረ ሲሆን፤የመጀሪያው በዩኒቨርሲቲው አስ/ተማ/አገ/ ም/ፕሬዝዳንት የሚመራ እና የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር፤የተማሪዎች መማክርት አባላትን እንዲሁም የተማሪ ክበባት ተወካዩችን የያዘ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ በዲኖች የሚመራ የየካምፓስ ቴክኒካል ኮሚቴ ነው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከሚገኙ ባለሙያዎች የተውጣጣ የህክምና ቡድን ተዋቅሯል::

ዓብይ ኮሚቴው በየካምፓሱ ያለውን ሁኔታ በአካል ዞሮ በማየት የቅድመ ዝግጅት ሥራውን ካስጀመረ በኃላ የሚከተሉትን ውሳኔዎች እና መልዕክቶችን አስተላልፏል

ተማሪዎች ከተከሰተው የኮሮና ሥጋት ጋር ተያይዞ በዚህ ወቅት ወደ ቤተሰብ መሄድ፤በጉዞ ወቅት ይበልጥ ተጋለጭነትን ስለሚጨምር በየጊቢያቸው ሆነው ከዩኒቨረሲቲው ሕክምና ቡድን እና ከበጎፍቃደኛ ተማሪዎች የሚሠጣቸውን መመሪያ መፈጸም አለባቸው፡፡

v የምግብ ሠዓትን በተመለከተ፤ የተማሪዎችን መጠጋጋት እና መጨናነቅ ለማስወገድ ሲባል ከዚህ በታች ያለው የሠዓት ማሻሻያ ተደርጓል፡

     ቁርስ- 1፡00 እስከ 3፡00

     ምሳ- 5፡30 እስከ 8፡00

     እራት-11፡00 እስከ 2፡00

v የ non-café ተማሪዎችን በተመለከተ ይህ ሁኔታ እስኪረጋጋ ድረስ የተለየ አሳማኝ ምክንያት ማቅረብ ካልቻሉ ጊዚያዊ የመመገቢያ መታወቅያ ተሰጥቷቸው በዩኒቨርሲቲው ካፌ መመገብ ይችላሉ፡፡

v    ተማሪዎች ከመምህራኖቻቸው የሚሰጧቸውን አሳይመንት እና ንባብ በአግባቡ መሥራት አለባቸው፡፡

v  የቤተ-መፅህፍት አገልግሎት እስክ ሌሊቱ 6፡00 የተራዘመ ስለሆነ፤ተማሪዎች መጨናነቅን ባስወገደ መልኩ በተለያየ ሰዓት እየገቡ መጠቀም ይችላሉ፡፡

v  ከጊቢ ውጭ መውጣት እና መግባትን በተመለከተ፤ከላይ እንደተጠቀሰው ወደ ቤተሰብ ወይም አቅራቢያ ላይ ወዳሉ ከተሞች መሄድ ፈጽሞ የተከለከለ ሲሆን፤ ይህንንም ለማስፈጸመም ተማሪዎች በአስገዳጅ ምክንያት ከጊቢ መውጣት ከፈለጉ መታወቂያቸውን በማስያዝ የሚወጡበት ሠዓት ተመዝግቦ ለአጭር ሰዓት ብቻ ከጊቢ ወጥተው መመለስ ይችላሉ፡፡

 ተማሪዎች በጊቢ ውስጥ የሚሠጡ የባንክ እና ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን በመጠቀም አላስፈላጊ የሆኑ የጊቢ ውጪ እንቅስቃሴዎችን ማቆም ይኖርባቸዋል፡፡

 v ተማሪዎች መውሰድ ስላለባቸው ጥንቃቄ ከጤና ባለሙያዎች እና ከታማኝ ምንጮች ብቻ መረጃዎችን በመቀበል፤ ከዪኒቨርሲቲው እና በግላቸው በሚያገኟቸው የንፅህና መጠበቂያዎች የግል ንፅህናቸውን በመጠበቅ እና በመረጋጋት ይህንን ጊዜ በጋራ ለማለፍ ጥርት ማድረግ አለባቸው፡፡

በመጨረሻም፤ትኩሳት፤ለመተንፈስ መቸገር፤ የትንፋሽ መቆራረጥ እና ሳል ካገጠመ ወይንም ይህንን ምልክት የሚያሳይ ተማሪ ካለ በነፃ ስልክ መሥመር 6929 ለደ/ብ/ብ/ሕ/ክ ጤና ቢሮ ጥቆማ መስጠት ይቻላል፡፡

$1v  በመተባበር፤በመደማመጥ እና የሚሰጡ መመሪያዎችን በስነምግባር በመፈፀም ይህንን ወቅት ማለፍ እንችላለን!!!

            

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ

Read 360 times Last modified on Thursday, 19 March 2020 20:07

Leave a comment

Make sure you enter the (*) required information where indicated. HTML code is not allowed.

Newsletter

Make sure you dont miss interesting happenings by joining our newsletter program.

Contact us

Armaye Assefa
Director, Corporate Communication & Marketing Directorate

  • Phone: +251462200341/+251462209331/+251462212720

Connect with us

We're on Social Networks.
Follow us & get in touch.