የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር HU/NCB/Mgarja./035/2006 BY

የጨረታ ማስታወቂያ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ መጋረጃ በአሎሚኒየም እና በነጭ PVC የተሰራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ከፌደራል ሀገር ውስጥ ገቢ ወይንም ከሌሎች ግብር ሰብሳቢ የመንግስት መ/ቤቶች ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን የተወጡና በመንግስት ጨረታዎች መካፈል የሚችሉ መሆኑን የሚገልፅ ማስረጃ፣ በፌደራል ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የመረጃ መረብ /website/ ላይ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ እና የሚጫረቱበት ዋጋ ከብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ) የሚበልጥ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የሚወዳደሩበትን ዕቃ አጠቃላይ ዋጋ 0.5% (ዜሮ ነጥብ አምስት በመቶኛ) በማስላት በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም CPO የጨረታውን ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ 50 (ሀምሳ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ወይም አዲስ አበባ አሜሪካን ኤምባሲ ፊት ለፊት የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ቅጥር ግቢ ከሚገኘው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጉዳይ አስፈፃሚ ቢሮ ቁጥር 352 መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቬሎፕ አድርገው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሸኔ 2 ቀን 2006 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
  5. ጨረታዎቹ ሰኔ 2 ቀን 2006 ዓ.ም ከቀኑ 8፡10 ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  6. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፉል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

ስልክ ቁጥር፡- (046) 221 26 47

              (046) 220 96 76

              (046) 220 96 78

ፋክስ፡-         (046) 220 51 63

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ

የመ.ሣ.ቁ. 05

ሀዋሳ

Newsletter

Make sure you dont miss interesting happenings by joining our newsletter program.

Contact us

Armaye Assefa
Director, Corporate Communication & Marketing Directorate

  • Phone: +251462200341/+251462209331/+251462212720

Connect with us

We're on Social Networks.
Follow us & get in touch.