የሲቪል ምህንድስና ት/ቤት የ2007 የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ቅበላ
- Details
- Category: Announcements
- Published on 21 August 2014
- Hits: 5150
ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሲቪል ምህንድስና ት/ቤት ለ2007 የትምህርት ዘመን አዲስ የድህረ ምረቃ ተማሪዎችን በ5 ፕሮግራሞች ማለትም፡-
- Construction technology and Management (COTM)
- Hydrolics Engineering
- Geotechnical Engineering
- Road and Transport Engineering
- Structural Engineering ተቀብሎ ማሠልጠን ይፈልጋል፡፡
በእያንዳንዱ ሃያ አምስት ለፕሮግራሙ ብቁ የሆኑ፣ የዩኒቨርስቲውን ደንብ እና መስፈርት ሊያሟሉ የሚችሉ ዕጩ ተማሪዎችን ብቻ ያስተናግዳል፡፡
የምዝገባ ቀን ከነሀሴ 20 - ጳጉሜ 3/2006 ዓ.ም
የምዝገባ ቦታ፡- ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ሬጂስትራር ጽ/ቤት እና የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ጽ/ቤት
የመግቢያ ፈተና የሚወጣበት ቀን መስከረም 10/2007 ጠዋት 3 ሰዓት
የመፈተኛ ቦታ፡- ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ብሎክ 129 የክፍል ቁጥር 102 እና 103 እንዲሁም የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ጽ/ቤት
የምዝገባ መስፈርት
- በዘርፉ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው
- ከቀድሞ መምህራን ወይም ከመስሪያ ቤቱ የድጋፍ ደብዳቤ በተጨማሪም
- በዩኒቨርስቲው የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና ማለፍ ይጠበቅበታል፡፡
1. ለኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ እና ማኔጅመንት
የመጀመሪያ ዲግሪ
- ሲቪል ምህንድስና
- ሲቪል እና ከተማ ምህንድስና
- ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት
ከሌሎች የትምህርት መስኮች ማለትም
- የህንጻ ኮንስትራክሽን
- አርክቴክቸር
- ሐይድሮሊክስ ኢንጂነሪንግ እና ኢንቫይሮመንታል ኢንጂነሪንግ
- የውሃ ሀብት ምህንድስና
- መስኖ ምህንድስና
በት/ቤቱ አድሚሽን ኮሚቴ ይወሰናል፡፡
2. ሮድ ኤንድ ሮድ ትራንስፓርተ ምህንድስና
- ሲቪል ምህንድስና
- ሲቪል እና ከተማ ምህንድስና
3. ጂኦቴክኒካል ምህንድስና
- ሲቪል ምህንድስና
- ሐይድሮሊክስ ምህንድስና
4. ሐይድሮሊክስ ምህንድስና
- ሲቪል ምህንድስና
- ሐይድሮሊክስ ምህንድስና
- መስኖ ምህንድስና
- ውሃ ሀብት ምህንድስና
- ውሃ አቅርቦት ምህንድስና
- የአካባቢ ምህንድሰና
- ሳኒተሪ ምህንድስና
5. ስትራክቸራል ምህንድስና
- ሲቪል ምህንድስና
ከዚህ በተጨማሪ አመልካቾች ከተማሩበት ተቋም እንዲሁም ከመስሪያ ቤታቸው የድጋፍ ደብዳቤ ማምጣት አለባቸው፡፡